ልጓም የሌለው አምባገነን መቆሚያው ገደል!

Published in: on May 17, 2021 at 6:06 pm  Leave a Comment  

ያኔ ነው መጨፈር (አዲስ ግጥም)

Published in: on December 19, 2020 at 11:03 pm  Leave a Comment  

ስለ ሃማ ቱማ በአሐዱ ሬዲዮ ላይ

Published in: on December 1, 2020 at 3:44 pm  Leave a Comment  

የኢትዮጵያ ፖለቲካ እውነታ በምኒልክ ወሰናቸው “የእንጆሪ ፍሬ” በሚለው ዘፈን ዓይን

Published in: on November 23, 2020 at 4:58 pm  Leave a Comment  

ዳኛው እማ የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝብ ነው (ኢያሱ አለማየሁ)

ክፍል 3

ክፍል 2

ክፍል 1

Published in: on November 15, 2020 at 11:41 pm  Leave a Comment  

ዳኛውማ የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝብ ነው (ክፍል ሁለት)

ኢያሱ ዓለማየሁ (ኢሕአፓ) –

ቀና ብሎ ሚገኝ ብርቅ እንጂ ነው ክብር፣
ተጎንብሶ ሚገኝ የወደቀ ነገር፤ የረከሰ ነገር።
ጸጋዬ ገብረ መድህን ደብተራው(በኢሕአፓ ነጻ ሜዳ)

በክፍል አንድ ለታደለች ኃይለሚካኤልና መላኩ ተገኝ (ሟቾች) በኢህ አፓ ላይ ላሰራጩት ሀሰትና ክስ ምላሽ ለመስጠት ሞክሬያለሁ። በኢሕአፓ ሲዘመትና ስንመልስ፣ ስመልስ የመጀመሪያችን አይደለም–የረጅም የትግሉ ውጣ ውረድ ተመክሮአችን ነው። በደጉ ዘመን ለመኢሶንም ለሌሎችም ምላሽ ሰጪ፤ መላኩ ራሱ አንዱ እንደነበር ትዝ ሲለኝ ዝቅጠት ሲመጣ ምን ያህል አዋራጅና አጥፊ እንደሚሆን እንደገና መገንዘብ የግድ ሆኗል።

በተያያዘ ግን እንደገና መነሳት ያለበት ዋና ጥያቄ ለምን በኢሕአፓ ላይ ዘመቻው አላቋርጥ አለ የሚለው ነው። ያው እንደሚጠበቀው የአጼው ስርዓት ናፋቂዎች ሁሉ ስርዓታችንየሚሉትን ተራማጁ ወጣት ለሽንፈት ስለዳረገው በኢሕአፓ ላይ ጥላቻ አላቸው። አሁንም ወንጀላቸውን ያልተረዱና ያላወራረዱ ደርጎችና የደርግ ርዝራዦች ዛሬም ለድርጅቱ ውድቀትና ጥፋትን ይመኙለታል። ኢሕአፓ አባቴን፤ወንድሜን ዘመዴን ገደለብኝ ብለው ቂም የያዙም አሉ። ሁሉም የራሳቸውን ጸያፍ ሚናና ታሪክ ማስታወስ ፈላጊዎች አይደሉም። ገንጣዮችና ጠባቦች በሞላ ኢሕአፓ ስለታገላቸውና ሀገር ስለጠበቀ አሁንም ሊያጠፉት ተፍጨርጫሪ ናቸው። የሀገር ሉዓላዊነትን ሲዳፈሩ ድርጅቱ አሌ ብሎ የታገላቸው ሁሉም–የቅርቦቹም የሩቆቹም አይወዱትም። የአሜሪካን የረጅም ዓመታት ቂምና የአረቦችን ጥላቻ ያጤኗል። ወያኔ ከ27 ዓመታት በላይ ኢሕአፓን ጠላት ብሎ ወግቶታል፤ ዛሬምቅጥረኞቹን አሰማርቶበት አለ፤ የስብሃት ነጋና ስዩም መስፍን ዓይን ያወጣ ጸረ ኢሕ አፓ ቅጥፈት ምስክር ነው። በአጭሩ ግን የኢትዮጵያ የቆዩም አዲሶችም ጠላቶች ጸረ ኢሕአፓ ናቸው። ከዚህ አንጻር የብዙ መጻሕፍት መቸክቸክ በደፈናው አዎንታዊ ሊባል የሚችል ቢመስልም አልሆን ብሏል። በበኩሌ ከ500 ገጾች በላይ ስለራሳቸው ጀብዱ ብለው ይሚቸከችኩት ይገርሙኛል። የረባ ስምሪት በሆነና መንፈሳዊ ቅናት ይዞን ቢሆንመልካም በነበረ። መደመር፤ ትውልድ እንዳይረሳ፤ አንጃ ወ ክሊኩ፤ የኢሕአፓ እንቆቅልሽ፤ ምስክርነት፤ አማራ ከየት ወደየት፤ የነጻነት ጎሕ፤ የደም ዘመን፤ ነበረ፤ የኢሕ አሠ ታሪክ፤ ማነው ዳኛው፤ ወዘተ… ወዘተ… መጽሃፍት ወረቀት ከመጨረስ ሌላ ለህዝብ ምንም ፋይዳ የላቸውም። ዋናው ችግራቸው ሀሰትን ይዘው ሚሸናከሉ መሆናቸው ነው። አዲሱን ትውልድ ሀቁን አይነግሩትም፤ስለራሳቸው ሞነጨሩ ሞነጫጨሩ እንጂ ለወጣቱየሚጠቅም መልዕከት የላቸውም። አንድ ሰው ዕድሜውም ሳይገፋና ምንም ታሪካዊ ስራ ሳያከናውን እንዴትስ የህይወት ታሪኬ ብሎ ከ 500 ገጽ በላይ ይከትባል ? በትግሉ ሂደት በስራ ብዙ የሀገር መሪዎችን አግኝቼ ነበር… ወዘተ ብዬ ብቸከችክ ከጉራ ውጪ ምን ሊጠቅም? ታዲያ ምን ይሁን ? ለዛሬው ወጣትና ትውልድ ሀቁ ተተርኮለት ለመጣበት ትግል በዕውቀትም እንዲታጠቅ ማድረግ እንጂ በትምህርት እሳት ነበርኩ፤ ሳድግ ጫማ አልነበረኝም ነበር ትረካን ምን ልዩ ያደርገዋል? ምንስ ነው ጥቅሙ?

ከዚህ በተያያዘ ደግሞ ጋዜጠኛ ናቸው የሚባሉት ጉዶች (ሟቾቹን በቅርቡ ቃለ መጠይቃ ያቀረቡላቸውን ሁለት ግለሰቦች በተለይ ይመለክታል) ስለሚጠይቋቸው ግለሰቦች ዘርህ ዘርሽ ማነው ከማለት አልፈው (በሽፍንፍን እርሶን ማን ልበል የሚለው ጥያቄ) ስለግለሰቦቹም በበቂ ታሪካቸውን አያውቁም። ሴትየዋ ወያኔነቷን ለሀገር አግልግያለሁ በሚል ሽፋን ልታልፈው ስትሞክር በዝምታ ያለፏት ሲሆን ሌላው ጠያቂ ሟቹን ሰውየ (መላኩ ተገኝ)ደግሞ የጠየቀው ስለ ወያኔ ደጋፊነቱና አገልጋይነቱ ሳይሆንሰውየው ያልነበረበትን በለሳን ጠርቶ በሠራዊት እዚያ ነበርክ ብሎታል። ሰውየውም የትጥቅ ትግሉን እናቁም ባይ መሆኑን ከቶም ሳያነሳ በለሳ ነበርክ ሲባል አልነበርኩም ብሎ ሀቁን ለመናገር አልደፈረም። ያልሆነን ነበረ፣ ነበርን ማለት የዘንድሮ ቀጣፊዎች ዋና መለያ ሆኗል። ኮለኔሉ ሲገበዝና የማያውቀውን አወቅኩ ሲልም ታዝበናልና ውሸት በገነነበት ስርዓትና አገዛዝ የፖለቲካው መድረክ በቀጣፊዎች ቢጣበብ የሚገርም አይሆንም። በዚህ አንጻር ሟቹ ሰውየ ስለ ኢሕአፓ ታሪክ መጻፍ ጉዳይ ቁም ንገር ሊባል የሚችል መናገሩን መካድ አይቻልም። ለምን የድርጅቱን ታሪክ አትጽፉም ባዮች ብዙ ናቸው። መጻፉ አልከበደም ግን ሀቁን መጻፍ እንደ መተርተሩ የሚቀልም አይደለም። ድርጅቱ አሁንም በትግል ላይ ስላለም ታሪክ ብሎ መገለጥ የሌለበትን አስፍሮ ራሱን ሊጎዳም መጠበቅ የለበትም–“ምስጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም” የሚለው ዛሬም አክብሩኝ ይላል። የኢሕአፓ ታሪክ ሰፊና የዳጎሰ ነውናም አንድ ወይ የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ የሚጽፉትም አይደል። ሀቁ ግን አሁንም እየታገሉ ባሉት የኢሕአፓ ልጆች እጅ እንጂ ድርጅቱን ከራቁ 30 አርባ ዓመት ባሳለፉ አንጃዎችና ከሀዲዎች እጅ አይደለም። አሲምባ ከተደረገው ትግል በበለጠ ሰፊ ትግል የተደረገው ሠራዊቱ ወደ ጎንደርና ጎጃም ከገባ በኋላ መሆኑን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል–በስፋትም በይዘትም። ይህ እንዳለ ሆኖም ታሪክን ለማስከበር በየጊዜው ስንጥር ዘመን አሳልፈናል። ነበር፣ ምስክርነት ወዘተ ብለው ሀሰት ላሳፈሩት፤ ዕንቆቅልሽ፣ የደም ዘመን ወዘተ.. ብለው የፈጠራ ጽሁፍን ላቀረቡት ምላሽ ሰጥተናቸዋል። አማራ ክየት ወደየት ላሉትም ገና ያኔ አማራ መሆን ፋሽን ባልሆነበት ጊዜ ምላሽ ሰጥተናል። ለወያኔ አሳን ወደ ተራራ፤ ከድጡ ወደ ማጡ፤ ከማጡ መስመጡ ወዘተ… በሚሉ ጽሁፎች ጥበታቸውንናጸረ ኢትዮጵያ መሆናቸውን ተችተን ብዙ ጽፈናል፤ አሉታዊ ሚናቸውን በጽሁፍም፣ በፍኖተ ራዲዮም አጋልጠን እርቃናቸውን ስናወጣ የዋሹትንም በዚያው ዜሮ አድርገነዋል። የሰማዕት ጓዶች ታሪክን ለመዘከርና ለማስከበር ይኸውም ዛሬም ውሸታሞቹን ሟቾች ቀጣፊዎች እያልናቸው ነው።

ስለ ኢሕአፓ ማንም አይጻፍ ባዮች ናቸው ይሉናል። በበኩሌ የዘንድሮ ወጣቶች እንደሚሉት የሚመቸኝ አነጋገር ነው–የማያውቁ፤ በድርጅቱም የትግል ታሪክ ብልጭ ድርግም ያሉ፤ ሊጽፉ ባይሞክሩ ደግ ነው። የማያውቁት ወይም ከድርጅቱ ከተለያዩት 40 ዓመት እያለፋቸው የድርጅቱን ወሳኝ ታሪክ ጻፍን ባይሉ በሚገባ የሚሻል ነው። ፍቅር ያሳብዳል ቢባልም በዚያው ልክ የዘንድሮ ፍቅር ሳይጀምሩት ያልቃል፤ ግለቱ የታጠበ መሀረብም አያደርቅም ተብሏል። የጌታቸውና ብርሃነ መስቀል ሚስቶች ለባሎቻቸው ያላቸውን ፍቅር በመጽሐፍ መልክ መግለጣቸው እንዳለ ሆኖ በዚህ አስታከው ታሪካችንን ሲክዱ፤ ሲያዛቡና በተለይም ውድ ህይወታቸውን ለትግል የሰዉትን ጓዶቻችንን ሲዘልፉ በዝምታ ልናልፍ ከቶም አንችልም። ሟቾቹ በየምክንያታቸው የብርሃነ መስቀል አምላኪዎች ናቸው። ውድ ሕይወትን መሰዋት ቀላል እንዳልሆነ ንገሩን ባይሉ ይመረጣል። ከዚህ አያይዛ ሴትየዋ ድርጅቱንበማይሆን መንገድ ከሳለች። ክሊኩ ለአባላት መርዝ (ሳያናይድ) እያደለ ሲያስገድል እርሱ ግን በዚህ አልተጠቀመም ብላለች። ያሳዝናል። በቂ ሳይናይድ ክኒን ኖሮን በነበረን ለሁሉም ታድሎ፤ ለነኢንጂነር አስማን፤ ማርቆስ ሐጎስ፤ተስፋዬ ደበሳይ፤ዮሴፍ አዳነ፤ ፍቅሬ ዘርጋው…ወዘተ… ተሰጥቷቸው በነበር ለአሰቃቂ ግብረ ስየልና አስከፊ ሞት ባልተዳረጉም ነበር። እሷ ባታውቀውም መርዝ ክኒን የሚሰጥበትም መመዘኛ ነበር። የሟቿ ባል እንደ ፊዴል ካስትሮ ተይዞ ታሪክ ነጻ ያወጣኛል (ሂስትሪ ዊል አብሶልቭ ሚ)ብሎ በፍርድ ቤት ለፍፎ ታሪክ ሲሰራና ህዝብ ተሰልፎ ሲያስፈታው ባይታየው (ባይቃዥ) ኖሮ፤ ደፋር ቢሆን ኖሮ ሳይናይድ ክኒኑን ውጦ ራሱን ሰውቶ በተስፋዬ ወልደሥላሴ ነፍሰ ገዳዮች ታንቆም ሊገደል ባልበቃ ነበር። ሳያናይድ መዋጥ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን መርዝ ለሌሎች ጓዶች ሰጥተውና ከሥቃይ ገላግለዋቸው እነሱ ግን ስየል ተቀብለው የተሰዉ ጓዶቻችንን ስትዘልፍ ተሳቀን፤ ባለጌ፣ ህሊና ቢስ ወያኔ ብንላት ሲያንሳት ነው። ደግሞ የማታውቀውን ዘሩን እንተውና ያስተማራትን ተስፋዪ ደበሳይን ለመዝለፍ ምንም የሞራል ብቃትና ማጠየቂያም አልነበራትም። ከመሞቱ በፊት ብርሃነ መስቀልን ሊያገኝ ፈልጎ ነበር፤ አቅዋም ቀይሮ ነበር በሚል ስለ ተስፋዬ ልታቀርብ የሞክረችውም አጥንቱ ይውጋትና ውሸቷን ነው። ብርሃነ መስቀል ለእኔ ላከው ያለችውን ደብዳቤ በተመለከተ በአጠቃላይ ሁኔታው ላይ ተነጋግረን ተስፋዬ ወደ አሲምባ እለፍ እኔም መጣሁ ባለው መሠረት ከሱዳን ወደ አሲምባ አልፌ ስጠብቀው የተሰዋ ቢሆንም በአንጃዎች ላይ ድርጅቱ የነበረውን አቅዋም ሙሉ በሙሉ ይደግፍ እንደነበር አውቃለሁ። ስታስበውስ ክሊክም አንጃም መሆን እንዴት ይገጥማል?

ለመቀጠል፤

ታደለች ወደ አዲስ አበባ እንደገባች በጻፈችልኝ ሁለት ደብዳቤዎች የተቸችልኝ ጉዳይ አንዱ የብርሃነ መስቀል ተክለሰውነት ያለችውን ሲሆን ሁለተኛው ደግም በሰሜን አሜሪካ ያሉ ጓዶች የስታሊንና ማኦ አዳናቂ የሆኑትን ተቃውማ ነበር። ይህን ደብዳቤዋን ለማዕከላዊ ኮሚቴን ጓዶች አስተላልፊያለሁ። ከዚያ ቀጥላ ደግም የጻፈችው ደብዳቤ ግልብጥ ብሎ የባሏን አቅዋም የሚያስተጋባ ሆኖ ሳገኘው ይህንንም ለአመራሩ ልኬ ምን ሆነች ስል ተስፋዬ የሰጠኝ መልስ፤ ክፍሉ ታደሰ በአዲስ አበባ በህቡዕ ከነበረው ባሏ ጋር አሳዘነኝ ብሎ እንድትገናኝ እንዳደረጋትና ባሏ እንደቀየራትም ነው፤ ወይም አቅዋም እንደቀየረች ነው። ከዚያ በኋላ በእሷና በእኔ በኩል የነበረው ግንኙነት አመቺ ባለመሆኑ ሲቋረጥ ለመጨረሻ ግን ብርሃነ መስቀል የጻፈልኝን ደብዳቤ ወደ ፈረንሳይ በምትበር የአየር መንገዱ አስተናጋጅ በኩል ልካልኛለች–ቀለጠ አለች እንጂ በአምጪዋ በኩል መልሴን ልኬያለሁ። ባለቤቱ እንደጻፈችው ክሊክ የሚላቸውን (ተስፋዬን፤ ክፍሉና ዘሩን) የሚከስ ነበር። ዋናው መልዕክቱ ከደርግ ጋር ተባብረን መስራት አለብን የሚል ሲሆን (በወያኔ ጊዜ ብቅ እንዳለው አንጃተበላን ይላል) ዋናው አጽንኦቱ በከተማ ጥይት መተኮስ ላይ ሳይሆን (“ተራማጅ መንግሥት ላይ ጥይት መተኮስ በርግጥም ስህተት ነው” ማለቱ ይታወሰኛል”) ከዋና ጸሃፊ ቦታው አለአግባብ መውረዱ ላይ ነበር። አንተም ጉባኤ የፖለቲካ ቢሮ አባል ብሎ መድቦህ በኮንፈረንስ ሊያነሱህ አይችሉም ካለም በኋላ ጉባኤ እንዲጠራና እስከዚያውም በዋና ጸሃፊ ቦታው እንዲቀጥል እንድጠይቅና እንድተባብረውና ጉባኤም እንዲጠራ እንድሰራ ጠይቆኛል። ከሠራዊቱ ከድተው ወደ ደርግ እጅ የሰጡት ሰባቶቹ ላይ ውግዘትና ሌላም እርምጃ እንዲወሰድ የፈለገውን አመራሩ ጉዳዩን መርምሮ እምቢ በማለቱና የሠራዊቱን አባሎችም አይመለስብን ባሉት መሠረት ወደሜዳ እንዳይመለስ መደረጉና በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ ይቀጥል ቢባልም ጸሃፊም ፖሊት ቢሮም አባል አለመሆኑ እንዳስቆጣው ግልጽ ነው። ሟቹ ሰውዬ (መላኩ ተገኝ) ብርሃነ ላይ ይህ ውሳኔ መወሰዱ ስህተት ነበር፤ ወደ መነጠልም ገፋፍቶታል ሲል ግለሰብ ከብዙሃን የድርጅት ውሳኔ በላይ ነው ሲል አስረግጧል። የብርሃነ ሎሌ መሆኑንም ሳይወድ አረጋግጧል ማለት ይቻላል። በመሥራች ጉባኤ የተገፋውና ሁላችንም ተስማምተን ዋና ጸሃፊ የሚል ሥልጣን እንዲኖር መደረጉ ስህተትና ጥፋት መሆኑ በተጨባጭ በተግባር ስለታየም የዋና ጸሀፊ ው ቦታ በአመራሩ /ኮንፈረንሱ ተሰርዟል። በሰራዊቱ የነበሩትበርካታ ጓዶች የብርሃነ ጠባይና አሰራር ጸረ ዴሞክራሲና ስታሊናዊ ነው ሲሉ መመስከራቸውም የሚካድ አይደለም። ይህን ዝንባሌ ቀደም ብለን አይተን ወደ ስልጠናና ሠራዊት ምደባ ሲወሰን እኒና ብንያም እሱን ልትቆጣጠሩት ትችላላችሁ ብለው መድበውን ብንያም በመንገድ በበረሃ ሲሰዋ እኔም ወደ መከካለኛ ምሥራቅ ስራ ተሰጥቶኝ ስቀር የታሰበው ሳይሆን ቀርቶ ጓዶችን የሚንቀው ብርሃነ ሊፈነጭ ችሎ የጓዶችን ተቃውሞ ማትረፉን ዛሬም በህይወት ያሉ የኢሕአሠ የያኔ አባላት ይመስክራሉ። ያኔ በሜዳ ገና ስላልነበርኩ የተባለውን አቀርባለሁ እንጂ ነበርኩ ባይ ምስክር አይደለሁም። ለደብዳቤው ግን በላኩት መልስ እስከመጪው ጉባኤ እንዲታገስና የግል እርምጃ እንዳይወስድ (“አንተንም ድርጅቱንም የሚጎዳ”) የሚል ማሳሰቢያን ያዘለ ሲሆን ከሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ መነሳቴንም እንደምደግፍ ገልጬለታለሁ። የደብዳቤውን ቅጅ በነበርኩበት አስቀምጬ ወደ ሜዳ አመራሩ ጋ ወስጄው ሁሉም የአንጃውን ግልጽ አቅዋም ሊያነቡት ችለዋል-36 ገጽ ሙሉ አቅዋም ማብራሪያ ነበርና። ዛሬ ዋናውተቃውሟችን በከተማ ተኩስ የሚለውን /የሚመለከት ነበር ብለው ሊመጻደቁ የሚሞክሩት ያዋጣናል ያሉት የኋላ መብራት አንጂ መሠረታዊ ልዩነቱ ከደርግ ጋር እንደ መኢሶን ሆነን እንስራ ወይስ በተቃውሞ ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግሥት ብለን እንቀጥል በሚለው ላይ ነው። ሽፍንፍንና ውሸት ለምን አስፈለገ?

ጊዜ ሲያስጠፉን እንጂ ይህ ሁሉ መነገሩ እምብዛም ለአዲሱ ትውልድ ወሳኝ ትምህርት ባልሆነም ነበር። ከዚያ ወቅት ትግል ጠቃሚው ተመክሮ ለትግል የተወሰደ የመደራጀት ጥረትና (ስልቱ፤ ራስ አነሳሽነቱ፤ ወኔውና ቆራጥነቱ ወዘተ) በተለይም ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግሥት አማራጭና አታጋይ መፈክርነቱ ነው። ይህ መፈክር–ለመጀመሪያ ጊዜ (ልክ እንደ ሙት ከተማ የትግል ስልት) በኢሕ አፓ የተነሳ ሲሆን እውን ሆኖ ኖሮ ቢሆን ሀገራችን ከዓመታት ስቃይና ሰቆቃ ትድን እንደንበር ምንም ጥርጥር የለውም። ዛሬም ከዘረኞች የቄሮ ግፍና ውጥንቅጥ በወጣን ነበር በጊዜ። ከዚህ አማራጭ ባሻገርም የህብረት ግንባር አማራጭን ከደርግ ጋር ተመሳጥረው ባቀረቡም ጊዜ ኢሕ አፓ ህብረት ለምን ተነስቶ የሚል ምላሽ ሰጠ የሚሉትም እንዲሁ ቅጥፈት እንደሆነ ይታወቃል። ዴሞክራሲ ይረጋገጥ፤ በህብረቱ ሁሉም ሀይሎች ይጠሩ ይሳተፉ ወዘተ ብለን መሆን ያለበትን ሂደት አብራርተን በአዎንታዊ አቀረብን እንጂ (የወቅቱ የዴሞክራሲያ ህትመት ላይ ሰፍሮ አለ) ህብረት አንፈልግም እምቢኝ አላልንም። ወደ ከተማ የራስ መከላከል እርምጃም ስንገባ (በወቅቱ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ባወጣው ጦርነት ታውጆብናል መግለጫ ማጠየቂያው በግልጽ ተቀምጧል) ከገጠር ወደ ከተማ የሚለውን መሠረታዊ መርህ ሽረናል ብለንም አልነበር። የከተማው ተኩስ የሀይል ሚዛን ሲለወጥም ተፋፍሞ መቀጠሉ ጉዳት ማድረሱን ድርጅቱ ራሱ በቋራ ሁለተኛው ጉባኤው አምኖ ግለሂስ የወሰደበት ሲሆንየመከላከል እርምጃ ግን ጥፋት ስህተት ነው ሊሉ የከጀሉት አንጃ ግራንጃዎችና የደርግ ወያኔ ቅጥረኞች ብቻ ናቸው። ዛሬም ቢሆን ለፍጅት ተዳርጎ በዘረኞች ሚታረደው ህዝብ ትጥቅ አንስቶ ራሱን መከላከል ይገባዋል ባይ መሆናችንን ሁሉም ሊያውቅ ይገባዋል።

ማንኛውም ሰው እናት አለው እንደተባለው ለአምባገእኖችም የሚወዷቸው እናቶች አሏቸው። ብርሃነ መስቀል ብዙ ቀና ጎኖች እንደነበሩት ሁሉ መጥፎ ጎኖችም ነበሩት። ራስ ወዳድና ራሱን አዳናቂ፤ የተክለሰውነት አምላኪ ስለነበርም በታሪክ ትልቅ ሰው ለመሆን ቦታ አለኝ ብሎ የሚያምን ነበር። በዚህም መሠረት የሕይወት ታሪኩን ለመጻፍ የሚረዱ ሰነዶችና መረጃዎችን ከሀገር ስንወጣ ይዞ ወጥቶ እንደነበር በቀጥታ አውቃለሁ። ብርህነ ማኦን ቻይና አግኝቶ ምክር እንደለገሳቸው (ቻይናም ሄዶ አየውቅም)፤ የሞዛምቢኩ ሳሞራ ማቬል ጋር ሆኖ ሞዛምቢክ እንደተዋጋ (በአልጄርስ ከነበሩ የአፍሪካ የነጻ አውጪ ድርጅት መሪዎች ጋር እንኳን ምንም ቀጥታ ግንኙነት አልነበረውም) ወዘተ ወዘተ የሀሰት ወሬ ይናፈስ ነበር። ዛሬ ካልካደች ባለቤቱም ብትሆን መጥፎ ዝንባሌ ነው ብላ ጽፋልኝ ነበር በቀጥታ። በአንጃነት ጌታቸው አልተሰለፈም ብላ ባሏን አዳንቃ ሚስትየዋ ብትጽፍም፤ ብርሃነ አብረው በአንጃነት መሰማራታቸውን አልደበቀም። ድርጅታችን ከመጀመሪያው የተክለ ሰውነት ጠር ነበርና (ከሰሜን ኮሪያም አንዱ ያራራቀን ጉዳይ ነው) ቻይና ማኦ ብለን የቻይና ጭፍን ተከታይ አልሆንም። ሟቹ ግለሰብ (መላኩ ተገኝ) የብርሃነ መስቀል ተክለ ሰብ አዳናቂና አምላኪ ነበር። ብርሃነ እንደ ተወርዋሪ ኮከብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ሚታይ ብርቅ ነው ብሎም ጽፏል። የቱኒዝያ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንትን የቡርጊባን ዝና የመንግሥቱ ራዲዮ ሲያናፍስለት “በቱኒዝያ ህዝብ ዓለም ይቀናል–ምክንያቱም ሁለት ጸሃዮች ስላለን፤ አንደኛው በሰማይ ላይ ሁለተኛው በመሬት ላይ ያለን ቡርጊባችን” ይል የነበረውን ያስታውሰኛል። የሚስትየዋ እንኳን መቸስ ማል ጎደኒ፤ የሰውየው ግን ምን ይባላል!! ጸረ ተከለ ሰውነት በመሆናችንና በጋራ አመራርና ሀላፊነት አጥብቀን ስለምናምንም በድርጅታችን ውስጥ አምባገነን ወይም አዛዥ ሊሆኑ የከጀሉትን ሁሉ ታግለን አክሽፈናቸዋል። ለእኛ ዴሞክራሲ ቃል ሳይሆን መመሪያችን መርሃችን ነውና አድሃሪ ስርዓትን ልንዋጋ ልንሰዋ ቆርጠን እያለን በድርጅታችን ውስጥ ህግና አላማ እንጂ የግለሰብ ተገዢ ልንሆን አልተዋጠልንም። አልፎም ድርጅትን እንደ ጣኦት አናይም ያልነው በድርጅት በርክተናል። ቆምጨጭ አልን፤ አዛዥ ናዛዥ ነን፤ ወዘተ ብለው የተኮፈሱት ተወጥረውና ወጥረው ፈንድተው በጎዳናው ለመቅረታቸው ብዙ መረጃ አለን። ሟቹ አንዱ ምስክር ነው። ለአመራር ቦታ ሲታጭ የመበላሸት የመጀመሪያ እርምጃውን መውሰዱን የሚያውቁት ያውቃሉ። የኢሕአፓ አመራር ኮሚቴ አባሎች አብዛኞቹ በትግሉ ተሰልፈው ተሰውተዋል እንጂ ለሌላው ሂድ ሙት እዝና መርዝ ዋጥ ብለው ሰጥተው ከመስዋእትነት የሸሹ አይደሉም። በመሆኑም ነው ሟቾቹ በሙጣጭ ሊመለመሉ የቻሉት። በታሪክ አጋጣሚ ለአመራር ቦታም በመብቃታቸው ድርጅታችንን በውሳኔ ሊያፈርሱ ጥረው ለጥቂት እንዳሸነፍናቸው የምንዘረዝረው ይሆናል። ይቀጥላል …

Published in: on November 5, 2020 at 2:23 pm  Leave a Comment  

ዳኛውማ ሁሌም የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝብ ነው


ኢያሱ ዓለማየሁ (ኢሕአፓ)

በቅርቡ የመጀመሪያው አንጃ መሪ የነበረው የብርሃነ መስቀል ረዳ ባለቤት የነበረችው የታደለች ኃይለሚካኤል “ዳኛው ማነው” የሚል መጽሃፍ ታትሞ ኢትዮጵያ በገበያ ላይ ውሏል። ጥራዝ ነጥቁ የወያኔ ኮለኔል ኢሕአፓን ማጥቂያ አንድ መረጃ ሙሉ ያገኘ መስሎት መጽሃፉን እንዳነበበ ሰው እየጠቀሰ በድርጅታችን ላይ ሊዘምትም ሞክሯል። የጌታቸው ማሩ ተቆርቋሪ ነኝ ሊል እንደሚቃጣው ማለት ነው። መጽሃፉ የወጣ ሰሞንም መላኩ ተገኝ የሚባል የእሷ ብጤ እንዲሁ በድርጅታችን ላይ ዘለፋና የሀሰት ክሶችን በቃለ መጠይቅ ሲደረድር ተደምጧል። የማያውቁትን ለማደናገር፤ የሚያውቁትን በሀሰት ለመክሰሰ ለመወንጀል ዘመቻው ሳያቋርጥ በኢሕአፓ ላይ ቀጥሏል ማለት ይቻላል።

በበኩሌ የግለሰቦቹን ስም ለማንሳት ቅንጣትም ፍላጎት ሳይኖረኝ ዓመታት አልፈዋል። ሁለቱም ለወያኔ ካደሩ ጊዜ ጀምሮ ለእኔ ሞተዋል። ገጣሚ አሊ ሁሴን አንጃዎችን ሟቾቹ የሚለውን እቀበላለሁና። ታደለች ከእሥር ወጥታ የወያኔ ሚኒስቴርና አምባሳደር ከሆነች ጀምሮ፤ ዛሬ ስላለፈው አቅዋሙ መተንፈስ ማይሻው ሰውዬ ደግሞ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወያኔን ደግፎ፣ ኢሕአፓን አውግዞ፤ ከዚያም በሲአዬ ቅጥረኛው በአብዱል አባ ቦራ በዩኒሴፍና ቀጥሎም ፓኖስ በተባለ የአሜሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት ተቀጥሮ የወያኔ የወጣለት ደጋፊ ሆኖ አዲስ አበባ ከገባና ኢህአዴግ ከወደቀ፣ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብሎ ራሱን ካዋረደ ጊዜ ጀምሮ ለእኔ ሞቷል። በዚህ ግድ ሆኖ ስማቸውን ሳነሳ እየቀፈፈኝ ነው። በአጭሩ፤ ዓይነታ ወያኔ፤ ለወደል ዘረኞች የተጎነበሰ ማንም ቢሆን ማን ኢሕአፓን ሊተች ቅንጣትም የሞራል ብቃት የለውምና ጉዳዩ በዚህ ሊያልቅ የሚገባው ነው ማለቱም ይቻላል።

ታዲያ ለምን ምላሽ አስፈለጋቸው? የተሰዉ የተለዩንና በህይወት የሌሉ ጓዶችን በሀሰት እያነሱ ስላወገዙና በሥልጣን ያለ የመሰለው ኮለኔልም ቅጥፈታቸውን ይዞ ጸረ ኢሕአፓ ዘመቻውን በማጧጧፉ በዝምታ የማይታለፍ ሆኖ በመገኝታቸው ነው። ይብላኝና ለቀባጣሪዎቹ አሁንም በህይወት ያለሁ ስለሆነ የሰማዕት ጓዶችን ክቡር ስምና የድርጅቱን ሀቀኛ ታሪክ መከላከልም ግዴታዬ ነው በሚልም ነው። እንደ ዘመኑ አልባሌ ጋዜጠኞችና ቃለ መጠይቅ አቅራቢዎች እርስዎን በመጀመሪያ ማን ልበል በሚል ዘር ቁጠርልን ሽፍንፍን ጥያቄ ገብቼ መልስ ልሰጥ ብችልም ስለነሱ አልሞክረውም። ኢሕአፓ ነበርኩ፤ ነኝና ዘር ቆጠራ መቸም አይሆንልኝም እንጂ ሟቾቹን በሚገባ አውቃቸዋለሁ። የእሷም የፍቅር ትረካዋ የማነበው መጽሃፍ ሆኖ ከቶም ባልተገኘ– ኢሕአፓን ባትነክካ ኖሮ፤ ወርቅ ጓዶችን ስም ልታጎድፍ ባትጥር ኖሮ። የሰውየውን መጻፍም አለማንበብ ብቻ ሳይሆን የሞቱ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ/ድምጽ ላለመስማት የወሰንኩት ገና ሲሞቱ፤ ወያኔ ሲሆኑ ነው። እንደ ጥላሁን ሆድ ይፍጀው ያልኩት ብዙ ነገር እንዳለ እነሱም ይረዱታል ብየ እገምታለሁ። ለነገሩ ውርቹ የጠና ባንዳና እንኩቶ አንጃ ከእኔ ምላሽ አያሻውም። ወደሚቀጥለው ከመግባቴ በፊት አንድ ሳላነነው የማላልፈው ነጥብ በኢሕአፓ ላይ መጽሃፍ ብለው ሚሞነጫጭሩት አብዛኞቹ ኢሕአፓን ዛሬ ሊተቹ ሲነሱ ድርጅቱን ከተለዩ ግን ቢያንስ ሰላሳ አርባ አመት እንዳለፋቸው ነው። አመራር ብለን ከሰጠናቸው ስም ውጪ በዕውን መሪዎቹን እንኳን አያውቁም።

ወደ ዋናው ትችት ከመግባቴ በፊት አንዳንድ – ዛሬ ቡራ ከረዩ፤ የባጥ የቆጡን መቀባጠርና ጥራዝ ነጠቅነት ሰፍኗልና– ጥያቄዎችን ሀቅን መሠረት አድርጌ ለማቅረብ ልሞክር። የድርጅት መሥራች፤ የሠራዊት መሥራች የሚባሉ ፈልተዋል።

በእርግጥ ኢሕአፓን በተመለከተ እነማን ናቸው በሀቅ መሥራቾች ሊባሉ የሚችሉት? ተመልምለው በጉባኤው የተገኙት? ከመጀመሪያው አመራር የተመረጡት? ከመጀመሪያው አደራጅና ቆርቋሪ የነበሩት?

በዚህ መስክ ብዙዎች በርካታ ውሸት ነዝተዋል። ማረም የእኔ ግዴታዪ ነው – ከመጀመሪያው እስካሁን በኢሕአፓነት አለሁና። በበኩሌ ለጥያቄው ብዙ ክብደት የምሰጠው አልነበርኩም– ከታሪክ አጋጣሚና አቅዋም ጋር የተያያዘ ነውና። የዛሬ የአመራር አባሎች ለምን በምስረታው አልነበራችሁም ብሎ ሊተች የሚነሳ ጅል ብቻ ነው። በኢሕአፓ መሥራች ጉባኤ በስህተት ተገኝተው ወዲያውኑ ወደመጡበት ሲመለሱ የከዱን አሉ። በጉባኤው ቢገኙም ለአመራር ቦታ ብቃት የላቸውም ተብለው ያልተመደቡም ነበሩ – የምንተቸውን ግለሰብ ጨምሮ።

የአንጃው ባለቤት በመጽሃፏ ባሏን ሁሉን አድራጊና ፈጣሪ አድርጋዋለችና የአይሮጵላን ጠለፋውንም ቢሆን እሱ የጠነሰሠው አለመሆኑን መጥቀስ እፈልጋለሁ። በወቅቱ የተማሪው እንቅስቃሴ ካለው ሚናና አቅም ውጪ ሁኔታው በመለወጥ ላይ ነውና የፖለቲካ ድርጅት መመስረት አለበት በሚል ተራማጅ ተማሪዎች መሰበሰብና መምከር ሲጀምሩ ባሏ ለፖሊስና ጸጥታ የተጋለጠ ስለነበር ቢያንስ እኔ በነበርኩባቸው የጥናት ስብሰባዎች ላይ አላየሁትም። ከዚህ በተያያዘ በተማሪዎች ማህበር የአድማ ኮሚቴ በምስጢር የሚሰሩ ሲመለመሉ ብርሃን መስቀልና አብዱል መጂድ ሁሴን ቀድመው የሚያዙ ስለነበሩ ያድማ ኮሚቴ አባሎችንም አያውቁም ነበር። የጠለፋውን ዕቅድ የወሰነውና የተስማማንበት ብንያም፤ ገዛኸኝ፤ እኔና አማኑኢል የተባለና ሳይቆይ የባከነ ተማሪ ነን። በእኔና ብንያም ቤት እየተፈራረቅን የመከርንበት ሲሆን ኃይለ የሱስን ብንያም ጠቁሞ ሲያመጣው አብዲሳን ደግሞ እሱ ጠቁሞ አምጥቶታል። የአጼው አገዛዝ በተማሪዎች ላይ ቁርጥ እርምጃ ሊወስድ ወስኗል የተባለውን ስንሰማ ደግሞ ብርሃነ መስቀል ቢለቀቅ አይበረክትምና አብሮ ከእኛ ጋር መውጣት አለበት፤ ይጠቅመናልም እሱ ብለን ሲፈታ አናግረነው ስለተስማማ አብሮን በጠለፋው ላይ ተሳትፏል። ለነገሩ ምግብ በመስራት ሆነ የአማርኛ ታይፕ ጸሃፊ በመሆንም በከፍተኛው ረድቶናል። ማደራጀት የሚለውን ስራ በሀገር ቤት ጸጋዬ ገብረ መድህን፤ ዋለልኝ፤ ጸሎተ ሕዝቅያስ እንዲቀጥሉት በሚልም እነሱም በዚሁ ተሰማርተዋል። መስፍን ሐብቱ ወደ በአልጄሪያ መጥቶ እዚያ ካለነው ተመካክሮ የማደራጅቱን ስራ አሜሪካ ሊሰራ ተወስኖ ወደዚያው ዘልቋል። የጊዜያዊ አደራጅ ኮሚቴ የተመሰረተው በአልጄርያ በነበሩት ጓዶች ሲሆን ወደ አውሮጳ በብራዚል የሀሰት ፓስፖርት ሄዶ የዛሬውን መስራች ነኝ ባይ የመለመለው (ከአሉታዊ ግምገማ ጋር) አሁንም በህይወት ያለው ገዛኸኝ ነው። በተመሳሳይ መንገድ ብንያም አዳነ በሞስኮ እህቱ ስለነበረች እሷ ጋ ሊያርፍና እዚያ የነበሩትን በድርጅት ጥረት አንዲይዝ ተልኮ እህቱን ንግሥትንም ባሏንም፤ ክፍሉ ታደሰንም ሊመለምል ችሏል። በምስረታ ጉባኤው የተገኘው ደስታ ታደሰ ሳይውል ሳያድር የከዳንና ከሷም ጋር በመኢሶን የተጠቃለለ ሲሆን ዓለሙ አበበም ወዲያውኑ ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ከመኢሶንና ከደርግ ተቃቅፏል። ክፍሉ ታደሰም ጊዜውን ጠብቆ የሠራዊትና ድርጅት በታኝ ሚና ይዞ ኢሕአፓን በከፍተኛ ደረጃ ጎድቷል።

በድርጅት ምስረታ ሂደት እንዴትስ ተሰራ? በአልጀርስ የነበርነው የሰራነው በጋራ ሀላፊነት በስብሰባ እየወስን ነበር። መኢሶኖች ሁሉን ሰሪ ብርሃነ መስቀል ነው የሚለውን አምነው ብዙ ተሳስተው ሰው አሳስተዋል። በአልጄሪያ የወጣው የጥላሁን ታከለ ጽሁፍ (በብሄር ጥያቄ ላይ) የጋራ ስራ ውጤት ሲሆን ብርሃነ መስቀል በራሱ ለብቻውም አልጻፈውም፤ ጥላሁን ታከለ የሚለውንም የሽፋን ስምም ብቻውን አላወጣ ወይም ሁሉም ተስማምቶበት ሳይሆን በብዙሃን ድምጽ ድጋፍ ነው። የምንተቸው ሰው ባልተሰናበተበት ምክንያት ለቀቅኩ ሲል ቢቀጥፍም (የከተማው ተኩስ ዋና ደጋፊ ነበርና) የጥላሁን ታከለን ጽሁፍ ለምሳሌ ያኔም ስታሊን ወዘተ ማለቱም ከግራ ሆኖ የማይጥመው ገዛኸኝ እንዳለ አልደግፍም አልቀበልም፤ ስታሊኒስት አማራጭም ነው ብሎ ከመጀመሪያው በግልጽ ተቃውሟል። በምስረታው ሂደት ዋና ሚና የነበረው ሌላው ዘሩ ክህሸን ሲሆን ከኢትዮጵያ ለትምህርት ብሎ ወደ አሜሪካ ሲጓዝ በአልጄሪያ አልፎ ተማክረን ስራውንም ለይተን ተስማምተንበት ወደዚያ መሄዱን ታደለች ስለማታውቅ የጻፈችው ባሏ – ከዘሩ ስለማይስማማ – የነገራትን በጭፍን ተቀብላ ነው። በዚህ ላይ ያኔ በአዲስ አበባ በተራማጅ ተማሪዎች አካባቢ የነበረውን ውዝግብና ችግር ማንሳቱ ተገቢ ይሆናል። ውዝግቡ የጀመረው በዩኒቨርስቲ አካባቢ ሲሆን በሀገር ውስጥ የማደራጀት ሥራ የተሰጣቸው እነ ጸጋዬ ታስሮ የነበረውን ዋለልኝን ለማስፈታት ጥረት ያደርጉ ነበርና ጥረቱን የሚያደናቅፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ በመቃወማቸው ነበር። የድርጅት ምስረታ ጥረት መጀመሩን የሚያውቁት እነ ዘሩና ጸጋዬ የተሰጣቸው መመሪያ ይፋ ፖለቲካ እንቅስቃሴን ትተው/ርቀው ስልችቷቸው ስራ ፍለጋ እንደገቡ እንዲያስመስሉና የህቡዕ ማደራጀቱን እንዲቀጥሉ ነበር። ስራ ሊይዙ ሲፈልጉ በየመስሪያ ቤቱ በጸጥታው ትዕዛዝ አንቀጥራችሁም ስለታባሉ የጊዜውን የጸጥታ ሀላፊ የሆኑ ሰዎች እንዲያናግሩት አድርገናቸው መጥተው ያናግሩኝ ባለው መሠረት ጸጋዬና ዘሩ ሄደው አርፈን እንስራበት ብለው አናግረውት የጸጋዬ ትዝ ባይለኝም ዘሩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀጥሯል። በሰፈር ልጅነት እሱን ሳይሆን እህት ወንድሞቹን አውቅ የነበረው ጌታቸው ማሩ እኛ ሀገር ልንለቅ ስንል ወደ ፖለቲካ የገባ ስለነበርና እነሱም በቀና መንፈስ ለመደራጀት እየሞከሩ ስለነበር የነዘሩና ጸጋዬ ስራ ፍለጋና ትምህርት እንማር አልዋጥላቸው ብሎ ተቀየሙና በመሃላቸውም ልዩነቱ ሰፋ። ተራማጆች ትምህርት ሲጨርሱ አድሃሪ እና ግለኛ ቢሮክራቶች መሆናቸው የተለመደ ነበርና የሚፈረድባቸውም አልነበሩም። ሁኔታው ከሮ ወደኋላም ኢሕአፓ ሊታወጅ ሲል ሳሙኤል ዓለማየሁ ካሜሪካ መልስ አስታራቂ ሆኖ አብዮትና (የነጌታቸው ቡድን) ዴሞክራሲያ/ኢሕአድ ቡድን ተዋህደው ኢሕአፓ ብለው ይፋ ሊሆኑ ችሏል። እኔና ብርሃነመስቀል ከስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ስንነሳ ጌታቸው ማሩና ሌሎች በስራ አስኪያጅ ኮሚቴውም በማዕከላዊ ኮሚቴም ገብተዋል። ዘረኛ ኮለኔል ሶስት ትግሬውች የፖለት ቢሮ ሀላፊ ሆኑ በሚል ሊዘቅጥ ሲሞክር ራሱን አዋረደ እንጂ ብርሃነመስቀል የሥራ አስኪያጁ የአመራር አባል ኮሚቴ ውስጥ አልነበረም። ኮለኔሉ የድርጅቱ ሊቀመንበር ብሎ አቅፎት የታየውም የዘንድሮ አንጃ መሪ እንኳን ሊቀመንበር ከማዕከላዊ ኮሚቴ ደጃፍ አካባቢም አልነበረም።

ዘሩ ወደ አሜሪካ እንዲወጣ የተባለውም ከቆየ አይበረክትም በሚል ሲሆን በአልጄሪያ ቆይታው ስናናግረው የተወሰነው በአሜሪካ ስለላ ድርጅቶች ዓይን የገባ ስለሆነ እነ መስፍን ሀብቱንም እንዳያስበላብን ከፖለቲካ የራቀ ጆሊ ጃክ ይባል የነበረው ዓይነት የሆነ መስሎ እንዲታይ ነበር። ይህንንም ማስጠንቅቂያና ሀሳብ የሰጠው “እኔ አውቀዋለሁ እንደልቡ ነው” ያለው ራሱ ብርሃነ ስለነበር ሴትየዋ የጻፈችው አስገርሞኛል። ዘሩ ከድርጅት እስኪሰናበት ድረስ ጸንቶ የሰራ ሲሆን ካንሰሩ ሊገድለው ሲልም አምስተርዳም ደውዬለት ሀገር ገብተህ ዘመድ አዝማድ ተሰናበት ስለው ምላሹ ቁጣና እነ ጸጋዬ ደብተራውን ወያኔ ፈታቸው እንዴ የሚል ብስጭት ነበር። አንዳንዶች አሁን አሜሪካ ያለ ፊልም አንሺው ኢትዮጵያዊ አዛውንት ዘሩን ቃለ መጠያቅ አቅርቦለት እንዲህ እንዲያ አለው ቢሉም ጉዳዬ ካለመሆኑ በላይ ለሀቅ ከቆመ ፊልም አንሺውም ዘሩ የተናገረውን ቅጂ አትሞ ቢያወጣና ሀቁ ቢታወቅ ደግ ይሆናል። ተሰናብቶ ከሄደ በኋላ ብንራራቅም ገነት ግርማ በወያኔ ስትያዝ ደውሎልኝ ስለ እሷም ሁኔታም ሆነ ስለመስራች ነን ባዮች የወያኔ ወዳጆች በዝርዝር ተነጋግረናል፤ ውይይት የጀመርነውና የቀጠልነውም ከዚህ ወዲያ ነው። ወደዚህ ሁሉ ዝርዝር የገባሁት በዘሩ ላይ ተነሱ የተባሉ በዚህም በዚያም ዘመቻ ስለከፈቱበት ነው። በማያውቀው ቀባጣሪ መሆን ልምዱ የሆነው ኮለኔል ለምሳሌ ጌታቸው ማሩን ያስገደለው ዘሩ ነው ብሎ ወጥ ሲረግጥ በዝምታ ማለፍ የሚቻል አይደለም። ለነገሩ ጌታቸው ማሩ በቅድሚያ አንጃ በሞት ይቀጣል የሚል ህግ ባለው ድርጅት ውስጥ ባልገባም ነበር – ለጥቆም ፖሊት ቢሮ አባል ስለነበር ይህ ህጋችን ይሰረዝ ባለም ብሎ ቀድሞ በተቃወመ ነበር እንደሌሎች። አልሆነም። ግደሉት ብሎ ኢሕአፓ እንደ ድርጅት አልወሰነም እንጂ ቢሆንም፣ በህግ መሠረት እስከሆነ ድረስ ማንም ሊከሰው መሠረት አይኖረውም። ኮለኔሉ ሚቀጥፈው ግን ጌታቸው ማሩ የተገደለው በዘሩ ነው በማለት ነው። መገደሉን ዘሩም፤ ጸጋዬም እኔም ተጽፎልን የተነገረን አሲምባ ሳለን ነው። በቦታው – ቢያንስ በከተማ — የነበረውና አሁንም የዛሬውን አንጃና ኮለኔሉን ደግፎ አዲስ አበባ ሚመላለሰውን ያውቃል ተብሎም የተጠቆመውን ግለሰብ ቢጠይቁ የተሻለ ይሆናል– ያልወሰነውን ሰው ወሰነ ብሎ ክመክሰስ። ለነገሩማ የድርጅት አባሎችን አጠፉ ብሎ በሚያውቁትና በተቀበሉት ህግ መሠረት ድርጅቱ ቢቀጣ ከዘመዶቻቸው ውጪ ስንቱን ሀገር ወዳድ የበሉት ዘረኞች ምን አገባቸው? ለአንጃ ተቆርቋሪ መስሎ የአሜሪካው ሹም ኮለኔል ሚብከነከነው ለፖለቲካ ፍጆታ ነው። ብዙዎቹ ከሳሾች – ሀፍረተ ቢስ ደርጎች፤ ባንዳዎችና መሰል አንጃዎች– ሰውየውንም ሚከሱትንም ግለሰብ ሆነ ድርጅቱን በሚገባ አያውቁም።

ሴትየዋ በአካል ሆነ በሌላ ዘሩን አታውቀውም – ጭራሽ – እሷም አልካደችም። ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይን ሆነ ሌሎችን ያታለለ ያደናገረ ግን እሱ ነው ስትል ግግም ብላለች። ለሟቹ ባሏ አለኝ ነበረኝ ባለችው ፍቅር መሠረት እሷ ጠላቶች ያለቻቸውን ሁሉ ብትጠላ መብቷ ነው። ደርግ ወድቆ ከእስር እንደወጣች ሳይገዳት መወየን በመረጠችበትም ጊዜ ለነታምራት ላይኔ አንድ ተለጣፊ መጽሄት ክሊኩ ይሰቀል ብላ ጸያፍ ጥሪ ማቅረቧን አልረሳንም። በጥፋት አጃቢዋ ደግም የሩቁን ከቅርብ ስናየው ብሎ ስም ጠርቶም ያወገዘን ከመሆኑ በላይ ወያኔ የሚለውን ክቡር ስም የኢሕአፓ ክሊክ በሕዝብ አስጠላው ብሎ ከሶ የብዙዎችን ተቃውሞ ያተረፈ ነበር። በቅርቡም ዘሩ “ማኒፑሌተር”(ሰውን አደናጋሪ ሸዋጅ) ነበር ሲል ተደምጧል – – እሱም ቢሆን እኔ እስከማውቀው ዘሩን በቅርቡ አያውቀውም። ተስፋዬ ደበሳይን የመሰለ የበሰለ ምሁር መናቅ ነው እንጂ ተስፋዬን ዘሩ ሆነ ማንም ባላመነበት የዘወረው ሰው አልነበረም። ያስተማራትን፤ ያነቃትን ተስፋዬን እሷም ከድታዋለች በአሳዛኝ!

እሷም ሆነ አጃቢዋም ሰውዬ ለምን ከድርጅቱ እንደተለዩ ሲያወሱ ጭራሽ ቅጥፈትን ማድረጋቸው አሳዛኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እውነት አይደለምና። በሚያስገርም ሁኔታ ሰውየው በከተማው ትግል ሁኔታ ልዩነት ኖሮት እንደሄደ ሊያስመስል ሲሞክር እሷም ደግሞ ልዩነቱ በከተማ ለምን ደርግና አጋሮቹ ላይ ተተኮሰ በሚል ተቃውሞ ወደክፍፍል እንዳመራ ልታሳምነንም ትሞክራለች። ቅጥፈት። ለእኔም ደብዳቤ ጽፎ መልስ እንዳላገኝም ትጠቅሳለች። እሱም በምን ተዓመር እንደሆነ ስለ ከተማው ውሳኔ ተጽፎለት ለእኔ ደብዳቤውን ልኮ ምን እንደደረሰ እንዳላወቀ ሊጠቅስ ሞክሯል። ለነገሩ ያኔም ቢሆን ተቃዋሞውን ባስታወቀኝ ነበር ግን ከሀገር ቤት ግንኙነት እሱን የማይመለክተው ስለሆነ ረስቶ ካልሆነ ለእሱ የጻፍለት አልነበረም። ከሆነም በክተማው የራስ መከላከል እርምጃ አልስማማም ማለት ይችል ነበር። ብሎም አያውቅም። በተጻራሪ ደግፎና የሰሜን አሜሪካ የነበሩ የያኔ ጓዶችን ተቃውሞ በአየለች ሽፋን ስም ሁለት በራሪ ወረቀቶችን (ፓማፍሌቶችን) አሳትሞ አውጥቷል። ምናለ ያኔ እንዲህ መስሎን እንዲህ ጽፈን ነበር ቢባል? በበኩሌ የራስ መከላከል እርምጀውን የደገፍኩ ስለነበር ዛሬም ቢሆን በበቂ አላደረግነውም – አሁንም ይደረግ ባይ ነኝ እንጂ – ምደብቀው ምንም የለኝም። እሷም እሱም ግን በገሃድ ይዋሻሉ። ብርሃነ መስቀልም ከመጀመሪያው ለከተማ አስፈላጊ ሊሆኑ ለሚችሉ አንዳንድ እርምጃዎች መዘጋጀት እንዳለብን ምንም ተቃውሞ አልነበረውም። ሜዳ ሊገቡ ካልቻሉት ስዩሜ ከበደ (ማታ ማየት ስለማይችል) ወይስ ዘርዓብሩክ (በውልደት ኤርትራዊ ስለሆነ ሻዕቢያ አላሳልፈውም ካለው) ማን የተሻለ ይሆናል በሚለው ምርጫም ላይ ስዩሜ ብሎ ከሌሎች ጋር ወሳኝ ነበርና በዚህ ላይ ምንም ያልተካፈለና ያላወቀ ድንግል አስመስለው ሊያቀርቡት ሚጥሩት ትክክል አይደለም። የሁሉም ተቃውሞ ዛሬ ውሎ አድሮ በከተማ ተኩስ ላይ ነው የሚሉት በቂ መረጃና ማጠየቂያ የለውም። በሚገባው እንበለው ካልን ውሸታቸውን ነው። መረጃውን እንቀጥልበት….

Published in: on November 3, 2020 at 9:25 pm  Leave a Comment  

ከታገሉ ፀንቶ፤ የጀግኖችን ገድል አድምቆ!!

Published in: on October 21, 2020 at 1:57 pm  Leave a Comment  

ግንቡም ተናገረ!

Published in: on September 21, 2020 at 5:36 pm  Leave a Comment  

ግንቡም ተናገረ!

Published in: on September 21, 2020 at 4:35 pm  Leave a Comment